Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

zerowaste

Zero Waste
Zero Waste

Zero Waste DC - Amharic (አማርኛ)

This page contains information about trash, recycling, and composting services in Washington, DC for Amharic speakers.

ይህ ገጽ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ስላለው የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት፣ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል እና ማዳበሪያ አመራረት አገልግሎቶች የተመለከተ መረጃን ይዟል።

Zero Waste DC [ዜሮ ቆሻሻ ያለባት ዲሲ]
የድር ጣቢያው ለዲስትሪክት ነዋሪዎች፣ የንግድ ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች እንዴት ቆሻሻን ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚችሉ፣ ቆሻሻን መቀነስ፣ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል እና ቆሻሻን ተጠቅሞ ማዳበሪያን ማምረት በተመለከተ እንደ በአንድ ጊዜ ቆም ተብሎ የሚገኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።

የመኖሪያ ቤት ቆሻሻ አሰባሰብ መረጃ እና ጥያቄዎች
በDPW-አገልግሎት ለሚያገኙ የመኖሪያ ቤት ቆሻሻ አሰባሰብ መረጃ ለማግኘት እባክዎ ወደ dpw.dc.gov ይሂዱ።

ምግብ ነክ ቆሻሻ አወጋገድ
የዲስትሪክት ነዋሪዎች በተመደቡላቸው የገበሬዎች ገበያዎች የምግብ ቆሻሻው በስብሶ ለማዳበሪያነት ጥቅም እንዲውል የምግብ ቆሻሻን መጣል ይችላሉ። የምግብ ቆሻሻ መጣያዎቹ ቦታዎች በሁሉም በስምንቱ ዋርዶች ላይ ቅዳሜና እሁድ ክፍት ይሆናሉ—ትክክለኛዎቹን ሰዓታት እባክዎ ያረጋግጡ።

መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል
ሁሉም የዲስትሪክት መኖሪያ ቤት ይዞታዎች በዲስትሪክቱ የመልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ዝርዝር መሠረት መልሰው ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ይጠበቅባቸዋል።

የምግብ አገልግሎት መሣሪያዎች መስፈርቶች
ከጃንዋሪ 1፣ 2017 ጀምሮ ምግብ ወይም መጠጥ በሚጣል የምግብ መገልገያ ዕቃ የሚያቀርቡ የዲስትሪክቱ የንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች ዳግም መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻሉ ወይም በስብሰው እንደ ማዳበሪያ ሊያገለግሉ የሚችሉ የምግብ አገልግሎት ማቅረቢያ ማሸጊያዎችን እንዲጠቀሙ ይጠበቅባቸዋል።

ለዲስትሪክት ሠራተኞች መረጃ
የአጠቃላይ አገልግሎቶች መምሪያ [Department of General Services (DGS)] በመንግሥት የሚተዳደሩ ሕንጻዎችን የቆሻሻ አወጋገድ እና የመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሥራ ውሎችን በበላይነት ያስተዳድራል።

ለጥያቄዎች፣ ችግሮችን ሪፖርት ለማድረግ፣ ወይም ቆሻሻ መጣያ እንዲቀርብ ጥያቄ ለማቅረብ እባክዎ ይህን ያነጋግሩ፦ [email protected].

ለትምህርት ቤቶች መረጃ
ተማሪዎችን፣ ሠራተኞችን እና ጎብኚዎችን ጨምሮ ቆሻሻቸውን መለየት እና ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲችሉ ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች፣ የሕዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች እና የግል ትምህርት ቤቶች በቀላሉ ሊደረስባቸው የሚችሉ ዳግም ሊታደሱ የሚችሉ ቆሻሻ መጣያዎችን እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል።

ለዲስ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች [DC Public Schools (DCPS)] የቆሻሻ አወጋገድ አገልግሎቶች የሥራ ውል የተሰጠው እና የሚተዳደረው በአጠቃላይ አገልግሎቶች መምሪያ [Department of General Services (DGS)] በኩል ሲሆን ደረጃቸው የጠበቁ መገልገያዎች በ DCPS Recycles! ፕሮግራም በኩል ይቀርባል

ግብዓቶች
ዲስትሪክቱ ተከታታይ የ Zero Waste DC [ዜሮ ቆሻሻ ዲሲ] ማስተማሪያ መሣሪያዎች እና ግብዓቶችን የሚከተሉትን ጨምሮ አዘጋጅቷል፦ ታታሚ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ የተተረጎሙ እውነታ ማስጨበጫ በራሪ ወረቀቶች እና ተጨማሪ ነገሮች።

የትርጉም አገልግሎት፦
በእርስዎ ቋንቋ እገዛ ከፈለጉ፣ እባክዎ በነጻ የአስተርጓሚ አገልግሎት እንዲያገኙ ወደ (202) 673-6833 ይደውሉ። ያለምንም ወጪ አስተርጓሚ ማግኘት እንዲችሉ ለደንበኞች አገልግሎት ተወካዩ እርስዎ የሚናገሩትን ቋንቋ ይንገሯቸው።

መገኛ አድራሻ
Office of Waste Diversion,(የቆሻሻ ልወጣ ቢሮ)፣
DC Department of Public Works (የዲሲ የሕዝብ ሥራዎች መምሪያ)
250 E Street, SW
Suite 430
Washington, DC 20003
zerowaste.dc.gov